ብሪክስ አፍሪካ ኢንዱስትሪዎችን እንድታስፋፋና ጥሬ ዕቃዎች ላይ በሀገር ውስጥ እሴት እንድትጨምር አቅም ይሰጣል - የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ

ሰብስክራይብ

ብሪክስ አፍሪካ ኢንዱስትሪዎችን እንድታስፋፋና ጥሬ ዕቃዎች ላይ በሀገር ውስጥ እሴት እንድትጨምር አቅም ይሰጣል - የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ

አኀጉሪቱን ብዙ ጊዜ በዕዳ ከሚያስሩት ምዕራባውያን ስምምነቶች በተለየ፤ ብሪክስ አፍሪካ ራሷ በምታቀርበው ቅድመ ሁኔታ እና ፍላጎቷ ላይ ተመሥርቶ የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎችን ያቀርባል ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ፒተር ክሪኤል ከህንዱ "ዊዮና" ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።

የብሪክስ አባል ሀገራት፤ አፍሪካውያን ጥሬ ዕቃዎችን ወደ ምዕራቡ ዓለም ከመላክ ይልቅ በሀገር ውስጥ እሴት መጨመር እንዲችሉ አኀጉሪቱን በኢንዱስትሪ ለማስፋፋት የሚያስፈልገውን የሙያ ክህሎት ያቀርባሉም ብሏል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ይህንን ለውጥ በግንባር ቀደምትነት እንደሚደግፉ እና አፍሪካ በፍትሐዊነት እንድትሳተፍና ድምጿም በእውነት እንዲሰማ ውስጣዊ ሀብቶች ወደ ውጭ ከመላካቸው በፊት እሴት ለመጨመር የብሪክስ ድጋፍን እንደሚሹ ክሪኤል አፅንዖት ሰጥቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0