የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ወደ ሕዳሴ ግድብና ሌሎች ሀይቆች የውኃ ትራንስፖርት ሊጀምር እንደሆነ አስታወቀ
16:33 12.09.2026 (የተሻሻለ: 16:34 12.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ወደ ሕዳሴ ግድብና ሌሎች ሀይቆች የውኃ ትራንስፖርት ሊጀምር እንደሆነ አስታወቀ
አገልግሎቱ የውኃ ትራንስፖርት ተዳራሽነትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ጀልባዎች ግዥና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።
የውኃ ትራንስፖርት አገልግሎቱን ከሕዳሴ ግድብ ሀይቅ በተጨማሪ ወደ ሌሎች አራት አዳዲስ ሀይቆች ለማስፋፋት መታቀዱን ይፋ አድርገዋል።
ሥራን ከማዘመን አኳያ አገልግሎቱ ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎችና የሀገር ውስጥ ባንኮች ጋር በመተባበር አዲስ ደንበኛ ተኮር ዲጂታል አሠራር መዘርጋቱም ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
