የኒው ዴልሂ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦ በዓለም እና ደቡባዊ ዓለም ጉዳዮች የብሪክስ ቀዳሚ አጀንዳዎች

የኒው ዴልሂ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦ በዓለም እና ደቡባዊ ዓለም ጉዳዮች የብሪክስ ቀዳሚ አጀንዳዎች
▪ ብሪክስ በታዳጊ እና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በዓለም አቀፍ ውሳኔ አሰጣጥ እና ተቋማት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ የሚጎለብትበት፣ ሁሉም የሚወከልበት፣ ፍትሐዊ እና አካታች የዓለም አቀፍ ሥርዓትን ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።
▪ የመሪዎች ጉባኤው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ የዓለም ባንክ እና የዓለም የንግድ ድርጅትን ጨምሮ የዓለም አቀፍ አስተዳደር መዋቅሮች፤ የግዜውን የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እውነታዎች በተሻለ ሁኔታ እንዲያንጸባርቁ እና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ድምፅ እንዲያጎሉ ሆነው እንዲሻሻሉ ጥሪ አቅርቧል።
▪ መግለጫው ዘላቂ ልማት፣ ድህነትን ማስወገድ እና አለመመጣጠንን መቀነስ የዓለም ዋና ቀዳሚ አጀንዳዎች እንደሆኑ ያመለከተ ሲሆን ብሪክስ የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳን ለማሳካት የሚደረገውን ትብብር እንደሚደግፍም አስፍሯል።
▪ ብሪክስ በውይይት፣ በዲፕሎማሲ እና በሰላማዊ የመፍትሔ መንገዶች ላይ ትኩረት የሰጠ ሲሆን በዓለም አቀፍ ሕግ መገዛት፣ የሲቪሎች ጥበቃ እና የቀውሶች መካካርን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች እንዲጠናከሩ ጥሪ አቅርቧል።
▪ መሪዎች የምግብ እና የኃይል ዋስትና፣ ዘላቂ የምግብና ቁሳቁስ አቅርቦት ሰንሰለት እንዲሁም በግብርና፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ላይ ያለውን ትብብር በማጠናከር የጋራ የልማት ተፎካካሪ ሁኔታዎችን ለመፍታት ያላቸውን ድጋፍ አድሰዋል።
▪ መግለጫው በጤና ጥበቃ ዘርፍ የሚደረግ ትብብር፣ የወረርሽኝ ዝግጁነት፣ የበሽታ መከላከል፣ የሕክምና ምርቶች አቅርቦት፣ የዲጂታል ጤና እና የጤና ሥርዓቶችን ማጠናከርን ትኩረት ሰጥቶታል።
▪ ብሪክስ የዲጂታል ሽግግር፣ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት፣ የሳይበር ደህንነት እና የቴክኖሎጂ ትብብርን አስፈላጊነት ያጎላ ሲሆን ትኩረቱንም ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አካታች እና ተደራሽ የዲጂታል ዕድገት ላይ አድርጓል።
▪ መግለጫው ለፍትሐዊ የንግድ ግንኙነት፣ የተናጠል የንግድ ገደቦች እንዲቆሙ እና በማደግ ላይ ያሉ ኢኮኖሚዎችን እና የዓለም ኢኮኖሚን ለማረጋጋት የጠነከረ ትብብር እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
