የደቡብ አፍሪካ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንግረስ ብሪክስ የሠራተኞች መብት እና ፍትሐዊ ንግድን እንዲያረጋግጥ አሳሰበ
የደቡብ አፍሪካ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንግረስ ብሪክስ የሠራተኞች መብት እና ፍትሐዊ ንግድን እንዲያረጋግጥ አሳሰበ
መጪው ጉባኤ ለሠራተኞች ጥበቃ ቁልፍ የሆኑ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ካደረገ፤ ብሪክስ ለደቡቡ ዓለም ሀገራት ጠንካራ የኢኮኖሚ ጥምረት የመፍጠር እና አሁን በሥራ ላሉ የንግድ ሞዴሎች ወሳኝ አማራጭ የመሆን አቅም አለው ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንግረስ ቃል አቀባይ ዛኔሌ ሳቤላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በኒው ዴሊሂ ከሚካሄደው የብሪክስ ጉባኤ አስቀድሞ ተናጋሪዋ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
🟠 የእነዚህን ወሳኝ የኢኮኖሚ ውጥኖች ትግበራ ለማፋጠን ቋሚ ሴክሬታሪያት ማቋቋም አስፈላጊ ነው።
🟠 አባል ሀገራቱ ጥምረቱን ከውጭ የኢኮኖሚ ጫናዎች ለመጠበቅ ከዶላር ጥገኝነት መላቀቅን ቅድሚያ መስጠት እና የጋራ የንግድ መገበያያ ገንዘብን ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።
🟠 የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ማጠናከር ለተባበረ አኅጉራዊ ዕድገት ወሳኝና የአፍሪካ ሀገራት ላልተመጣጠነ ቀጣናዊ ዕድገት መፍትሄ ለመስጠት የብሪክስን ስትራቴጂዎች እና ንግድ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል።
🟠 በተጨማሪም የአዲሱ የልማት ባንክ የብድር ሥርዓት ትውልዳዊ የዕዳ ወጥመዶችን ሳይፈጥር፤ የተሻለ የሥራ ካባቢን እና በቂ መተዳደሪያ ደመወዝን የሚያበረታታ መሆን አለበት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X