- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአፍሪካ አረንጓዴ ጎህ፡ የማዕድን እሴትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት

የአፍሪካ አረንጓዴ ጎህ፡ የማዕድን እሴትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ከዓለም አቀፉ ማዕድናት ክምችት ውስጥ ወደ 30 በመቶ ገደማ የሚሆነውን ድርሻ የምትይዝ ቢሆንም፣ ከእነዚሁ ማዕድናት ማጣራትና ማቀናበር ከሚገኘው ዓለም አቀፍ እሴት ውስጥ የምታገኘው ከ3 በመቶ ያነሰውን ብቻ ነው።

ስለ ፍትሐዊ የኃይል ሽግግር ስናወራ ስለ ኢኮኖሚያዊ ፍትሕም ማሰብ አለብን። እሴት ሊረጋገጥ የሚችለው ደግሞ ጥሬ ዕቃ ከመላክ ይልቅ ማዕድናትን በማጣራት፣ በማቀናበርና በማምረት ነው፤ አረንጓዴ ሽግግርን ከልማት መነጠል የለብንም” ሲሉ ማሪት ቅጣው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። የመጀመሪያው፣ አፍሪካ ከአዳዲስ ዓለም አቀፍ ጥምረቶች እና ከሻንጋይ የትብብር ድርጅት የምታገኛቸውን ትምህርቶች ከወራቤ ዩኒቨርሲቲው የምጣኔ ሀብት መምህር መሐመድ ኢሳ ጋር የምንዳስስበት ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ አፍሪካ ልማትና የድህነት ቅነሳን ሳታስተጓጉል ወደ ንጹሕ የኃይል አማራጭ የምታደርገውን ሽግግር ይመለከታል። በጉዳዩ ላይ ሪቻርድ ሚዩንጊ (ዶ/ር) እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ማሪት ቅጣው አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።


ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerAfripods SpotifyPocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0