ሱዳን ለሕዝብ ጥቅም የሚበጁ የብሔራዊ ውይይት ውጤቶችን ለመተግበር ቁርጠኛ ናት - አል-ቡርሃን

ሰብስክራይብ

ሱዳን ለሕዝብ ጥቅም የሚበጁ የብሔራዊ ውይይት ውጤቶችን ለመተግበር ቁርጠኛ ናት - አል-ቡርሃን

ውይይቱ ወታደራዊ ተሳትፎ እንደማይኖርበትና የፖለቲካ እንዲሁም የሲቪል ኃይሎችን ብቻ እንደሚያካትት፤ የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ለሱዳን የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች ተናግረዋል፡፡

አክለውም ተሳታፊዎቹ ሀገሪቱን በፍትሕና በእኩልነት ላይ ለመገንባት የሚሹ አካላት መሆናቸውን አብራርተዋል።

ከአል-ቡርሃን ንግግር የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

◻ የመሣሪያ ማዕቀብ፦ በአሜሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የቀረበው የመሣሪያ ማዕቀብ ውሳኔ "አይፀድቅም"፤ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይም ምንም ዓይነት ተፅዕኖ አይኖረውም ሲሉ አረጋግጠዋል።

◻ ከጦርነቱ በኋላ ምንም ዓይነት ታጣቂ አይኖርም፦ መሣሪያ በማንሣት የሚጠቀም ቡድን እንደማይኖር የገቡትን ቃል ያደሱ ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አሸባሪ ሚሊሺያ በሱዳን መንግሥት ውስጥ ምንም ዓይነት ሚና እንደማይኖረው አበክረዋል።

◻ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም፦ በወቅቱ የተከሰተው ድርጊት መፈንቅለ መንግሥት ሳይሆን የአብዮቱን መንገድ ማቅኛ እንደነበር ገልጸው፤ የመጀመሪያው የሐምዶክ መንግሥት ሀገር የመገንባት ጥረት አልተሳካም ብለዋል።

◻ ውድቅ የተደረገው ስምምነት፦ የቀድሞው የሐምዶክ ሚኒስትሮች አስፈጻሚውን አካል በመቆጣጠር ለ10 ዓመታት ለመግዛት ያዘጋጁትን ስምምነት እርሳቸው ውድቅ እንዳደረጉት ይፋ አድርገዋል።

◻ የአሜሪካ ጥሪ፦ አሜሪካውያን ወደ ሱዳን መጥተው በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ እንዲገመግሙ ጥሪ ማቅረባቸውንና ጥሪው እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ ገልጸዋል።

አል-ቡርሃን የሱዳንን ሕዝብ "የክብር ተጋድሎ" አድንቀው፤ መስዋዕትነቶቹ ሊመዘገቡ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። ከሱዳን ጎን የቆሙ ወዳጅ ሀገራትንም አመሥግነዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0