ኢጋድ ኢትዮጵያን የምሥራቅ አፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የልምድ ማዕከል የሚያደርግ አዲስ ቀጣናዊ ትብብር ሊመሠርት ነው

ሰብስክራይብ

ኢጋድ ኢትዮጵያን የምሥራቅ አፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የልምድ ማዕከል የሚያደርግ አዲስ ቀጣናዊ ትብብር ሊመሠርት ነው

የምሥራቅ አፍሪካ በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ)፤ አባል ሀገራቱ ከኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ልምድና ዕውቀት የሚጋሩበት አዲስ ቀጣናዊ የትብብር ማዕቀፍ የመመሥረት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።

የድርጅቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ፤ “ኢትዮጵያ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እና በፋይናንስ ዘርፎች የሰው ሠራሽ አስተውህሎትን ለመጠቀም ያሳየችው ድንቅ ስኬት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ማሳያ እና ምሳሌ የሚሆን ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታየ ግርማ፤ ኢትዮጵያ ዕውቀቷን፣ ልምዷን እና ሙያዊ አቅሟን ለቀጣናው ሀገራት ለማካፈል እንዲሁም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው የዘገበው።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0