የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በፔትሮሊየም እና ተፈጥሮ ጋዝ ትምህርቶችና ምርምሮች ልዩ የልህቀት ማዕከል ተደረገ
15:11 10.09.2026 (የተሻሻለ: 15:14 10.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በፔትሮሊየም እና ተፈጥሮ ጋዝ ትምህርቶችና ምርምሮች ልዩ የልህቀት ማዕከል ተደረገ
ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበት አከባቢ ለኃይልና ኢነርጂ ዘርፍ ዕድገት እጅግ ተስማሚና ምቹ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ስላለው ውሳኔው መተላለፉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮውን ለማስፈጸም የኢትዮጵያ ፔትሮሊየምና ኢነርጂ ኢንስቲትዩት የተሰኘ ልዩ ተቋም በመመሥረት በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሥራ ያስጀምራል።
ተቋሙ በዘርፉ በምርምር የተደገፈ ዕውቀትን የማፍራት፣ ልዩ የክህሎት ሥልጠናዎችን የመስጠት እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገትን የማፋጠን ኃላፊነት ተጥሎበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X