የኡጋንዳ ንዑስ ብሔራዊ ግዛት የንጉሥ ኦዮን ህልፈት ተከትሎ ጋዜጠኛውን አዲሱ ንጉሥ አድርጎ ሰየመ - መገናኛ ብዙኃን

© telegram sputnik_ethiopiaየኡጋንዳ ንዑስ ብሔራዊ ግዛት የንጉሥ ኦዮን ህልፈት ተከትሎ ጋዜጠኛውን አዲሱ ንጉሥ አድርጎ ሰየመ - መገናኛ ብዙኃን
የኡጋንዳ ንዑስ ብሔራዊ ግዛት የንጉሥ ኦዮን ህልፈት ተከትሎ ጋዜጠኛውን አዲሱ ንጉሥ አድርጎ ሰየመ - መገናኛ ብዙኃን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.09.2026
ሰብስክራይብ

የኡጋንዳ ንዑስ ብሔራዊ ግዛት የንጉሥ ኦዮን ህልፈት ተከትሎ ጋዜጠኛውን አዲሱ ንጉሥ አድርጎ ሰየመ - መገናኛ ብዙኃን

የቤተ-መንግሥቱ አልጋ ወራሽ ኮሚቴ በመንግሥታዊው የዩቢሲ ብሮድካስት ጋዜጠኛና ኤዲተር የሆኑትን ልዑል ኤድዋርድ ሩኪዲ ኪጃናንጎማን አዲስ ንጉሥ አድርጎ መምረጡን አስታውቋል።

ኡጋንዳ ሕገ-መንግሥታዊ ሪፐብሊክ ብትሆንም፤ ባለፈው ወር በ34 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኦዮ ኒይምባ በምዕራብ ኡጋንዳ የምትገኘውን እና ጥንታዊ ባሕላዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ያላትን የቶሮ ግዛት ሲገዙ ቆይተዋል።

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል በሚደረገው ትግል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የበጎ አድራጎት አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ኦዮ ኒይምባ፤ በጊነስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ መረጃ መሠረት እ.አ.አ በ1995 ወደ ዙፋን የወጡ የዓለማችን ወጣቱ ንጉሥ ነበሩ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0