ብዝሃ ቋንቋን ማስፋፋት ሀገራዊ አንድነትን ይገነባል - ካሜሮናዊ ባለሙያ
09:04 10.09.2026 (የተሻሻለ: 09:14 10.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ብዝሃ ቋንቋን ማስፋፋት ሀገራዊ አንድነትን ይገነባል - ካሜሮናዊ ባለሙያ
የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች አፍሪካውያን የቀደምቶቻቸውን እውቀትና ባሕል ጠብቀው እንዲያቆዩ ያስችሏቸዋል፤ ይህ ካልሆነ ግን እውቀቱ ሊጠፋ ይችላል ሲሉ ናዴዥ ማካ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ካሜሩን ከፈረንሳይኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች በተጨማሪ ወደ 280 የሚጠጉ ሀገር በቀል ቋንቋዎች አሏት። ይህ የብዙ ቋንቋዎች ባለቤትነት እንደየክልሉ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ወይም ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ማኀሰበረሰቦች መካከል የሚፈጠርን "የአድልዎ ስሜት" ለማስወገድ ይረዳል ሲሉ የፔዳጎጂ ተመራማሪው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ብሔራዊ ቋንቋዎችን እንዴት በስፋት ማስተማር ይቻላል?
መምህራንን ማሠልጠን፦ እውቀትን ለተማሪዎች በተሻለ መንገድ ማስተላለፍ ያስችላል፣
የትምህርት ስርዓቱን ማበልጸግ፦ የብሔራዊ ቋንቋዎች ጥናት "ጉዳዩ ከማይመለከተው የትምህርት ዓይነት" ጋር እንኳ ተካቶ መሰጠት አለበት።
ለዚህ ደግሞ ውድ የሆኑ የመማሪያ መጻሕፍት ወይም የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች አያስፈልጉምፀ ሲሉ አጠቃለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X