ቴክኖሎጂ እያደገ ሲሄድ፤ ማጭበርበሮች እና የሳይበር ወንጀሎችም አብረው ይበልጥ እየረቀቁ ይሄዳሉ - ደቡብ አፍሪካዊ ተመራማሪ
08:33 10.09.2026 (የተሻሻለ: 08:34 10.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቴክኖሎጂ እያደገ ሲሄድ፤ ማጭበርበሮች እና የሳይበር ወንጀሎችም አብረው ይበልጥ እየረቀቁ ይሄዳሉ - ደቡብ አፍሪካዊ ተመራማሪ
"የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሣሪያዎች፣ የፊት ገጽታ መጓዳኛ፣ ዲፕፌክ እንዲሁም የረቀቁ ጥቃቶችን በመጠቀም መረጃዎችን የሚሰርቁ በርካታ የሳይበር ወንጀሎችን እያየን እንገኛለን" ሲሉ የፎረንሲክ ሳይንቲስት ክሬግ ፔደርሰን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
የጥቃቱ ሰለባዎች ቁጥር እየጨመረ በሄደበት ወቅት አሳሳቢው ጉዳይ ሪፖርት የማይደረጉ ወንጀሎች መብዛታቸው ነው ያሉት ባለሙያው፤ "በሕግ አስከባሪ አካላት ላይ ጥልቅ እምነት በማጣታቸው ምክንያት ሰዎች ጉዳታቸውን ዝም ብለው አምነው በመቀበል ያልፉታል" ሲሉ አብራርተዋል።
"በመሣሪያዎቻቸው ላይ ባለ ሁለት እና ባለ ሦስት ደረጃ የማረጋገጫ ሥርዓት የሚጠቀሙ እንዲሁም የራሳቸውን የግል መረጃ አሳልፈው ሲሰጡ ይበልጥ ጥንቃቄ የሚያደርጉ ዜጎችን መገንባት አለብን።"
በዲጂታል ባንክ ዘርፍ የሳይበር ወንጀለኞች የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን፣ የፊት ምስል መቀያየሪያዎችን እና በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የተሠሩ የሀሰት ሰነዶችን በመጠቀም ሥርዓቱን እያዛቡ እንደሆነ ፔደርሰን ተናግረዋል።
የደቡብ አፍሪካ ባንኮች ግን "ለእነዚህ ስጋቶች ፈጣን ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ" ሲሉ አክለዋል።
የተደራጁ የሳይበር ወንጀል ቡድኖች ለምን እየጠነከሩ እንደመጡ እና ተገልጋዮች ለምን ለጥቃት ተጋላጭ እንደሆኑ ለመረዳት ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X