ጳጉሜን፦ ትርጉም እና ከምዕት ዓመታት በህዋላ የሚኖራት ለውጥ
08:02 10.09.2026 (የተሻሻለ: 08:04 10.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጳጉሜን፦ ትርጉም እና ከምዕት ዓመታት በህዋላ የሚኖራት ለውጥ
"ጳጉሜን" የዕብራይስጥ ቃል መሆኑን እና ትርጉሙም ተጨማሪ ዕለታት ወይም ቁጥር ማለት እንደሆነ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት መምህር ሊቀ ጠበብት አማረ ተፈረደው ይናገራሉ፡፡
ጳጉሜን በዘመነ ዮሐንስ ብቻ እንዴት ስድስት ዕለታትን እንደምትይዝ የአቡሻህርን አስተምህሮ ጠቅሰው አስረድተዋል።
ኬንትሮስን መሠረት በማድረግ ከሰከንድ ወደ ደቂቃ፣ ከደቂቃ ወደ ሰዓት፣ ከሰዓት ወደ ቀን፣ ከቀን ወደ ዓመት የሚደረገው ሽግግር እና የዘመን ዑደት የጳጉሜን ቀናት ከ 6 ወደ 7 እንደሚያሳድጋቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ አብራርተዋል፡፡
"ከ600 ዓመት በኋላ,ሰባት የምትሆንበትም አጋጣሚ አለ” ሲሉም አክለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X