- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

በብራና የተጻፈ፡ የኢትዮጵያ ሕያው የሥልጣኔ መዝገብ

በብራና የተጻፈ፡ የኢትዮጵያ ሕያው የሥልጣኔ መዝገብ
ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን ስለ አፍሪካና ኢትዮጵያ ጥንታዊ የእውቀት ሀብት ያላቸው ግንዛቤ አሁንም ዝቅተኛ በሆነበት በዚህ ዘመን፣ የአህጉሪቱን ሕያው የሥልጣኔ መዝገብ በዲጂታል አማራጮች አዘምኖ ለዓለም ማሳወቅ የህልውና ያህል አስፈላጊ ጉዳይ ሆኗል።

ምዕራባውያን “የብራና አሰራር ክህሎቱ የላችሁም” የሚል ሙግት ያነሳሉ። የእኛ ዓላማ ግን ዳግም መስራት እንደምንችል ማሳየት ነው። በተጨማሪም በቂ ጥናት ስላላደረግን እንጂ በየገዳማቱ ከተሰረቀብን በላይ ብዙ መጻሕፍት አሉን” — ትንሳኤ ተስፋሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት።

የዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት ከነሓሴ 28፣ 2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 3፣ 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና መጻሕፍት ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ የሐመር ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትንሳኤ ተስፋሚካኤልን እና የፕሮጀክት ማናጀሯን ቃልኪዳን ብርሃኑን አነጋግረናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerAfripods SpotifyPocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0