ኢትዮጵያ ከፊት ለፊቷ የተደቀነውን የኤል ኒኖ አደጋ ለመቋቋም የአየር ንብረት ትንበያዎችን መሠረት ያደረገ ጠንካራ የጤና ስርዓት መገንባት ይገባታል ተባለ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከፊት ለፊቷ የተደቀነውን የኤል ኒኖ አደጋ ለመቋቋም የአየር ንብረት ትንበያዎችን መሠረት ያደረገ ጠንካራ የጤና ስርዓት መገንባት ይገባታል ተባለ

የአየር ጠባይ ለውጥ ከጤና ጋር የጠበቀ ቁርኝት አለው ያሉት የኢትዮጵያ ሜትዮሮሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈጠነ ተሾመ፤ “የአየር ጠባይ መለዋወጥ በውሀ ወለድና በሌሎች በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ስርጭት እንዲሁም በግብርና ምርቶች ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ያሳድራል” ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት ትኩረቱን የአየር ጠባይ ትንበያዎችን ወደ እውነተኛ የጤና እና ሥርዓተ-ምግብ እርምጃዎች መቀየር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ አድርጎ፤ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተካሄደ ዐውደ ጥናት ላይ እንደሆነ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በበኩላቸው፤ የኢንስቲትዩቱ የምርምር ቡድኖች በአየር ንብረት፣ በአየር ጥራት እና በፖሊሲ ውጤቶች ላይ የሚታዩ ውስብስብ ሁኔታዎችን እየገመገሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ኢኒስቲትዩቱ መረጃዎቹን ወደ ፖሊሲና ተግባራዊ እርምጃዎች ለመቀየር የሚያስችል "የአየር ንብረት እና ጤና አስተዳደር የእውቀት ማዕከል" ማቋቋሙንም ዶ/ር መሳይ አስታውቀዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0