ሌሎች ሀገራትን ይኮንናሉ ብላችሁ አትጠብቁ - የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትር በደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ የስደተኞች ትብብር ዙሪያ
10:32 09.09.2026 (የተሻሻለ: 10:34 09.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሌሎች ሀገራትን ይኮንናሉ ብላችሁ አትጠብቁ - የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትር በደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ የስደተኞች ትብብር ዙሪያ
ደቡብ አፍሪካ የድንበር ትብብር እና የስደተኞች ፍሰትን ለመቆጣጠር ከጎረቤቶቿ ጋር በዲፕሎማሲያዊ መስመሮች በኩል እንደምትሠራ የደቡብ አፍሪካ የስደተኞች ጉዳይ የሚኒስቴሮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ምማሞሎኮ ንኬንሳኒ ኩባዪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል።
የሀገሪቱ የድንበር አስተዳደር ባለሥልጣን በጋራ ኦፐሬሽኖች እና መረጃ ልውውጥ ረገድ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር እየሠራ ይገኛል ሲሉ አክለዋል።
"የጋራ ዕቅዶቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲኖር ለማድረግ ያለሙ ናቸው።"
ከታህሳስ በፊት የክልሉን የስደተኞች ጉዳይ ለመፍታት የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የስደተኞች ጉባኤ "መጠራት አለበት" ሲሉ ኩባዪ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከባለሥልጣኗ የተሰጡ ተጨማሪ ዝርዝር አስተያየቶችን ለማግኘት የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ያዘጋጀውን ቪዲዮ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X