ማልዲቭስ የቻጎስ ደሴቶችን ሉዓላዊነት በተመለከተ ለዩናይትድ ኪንግደም ስጋቷን ገለጸች

© telegram sputnik_ethiopiaማልዲቭስ የቻጎስ ደሴቶችን ሉዓላዊነት በተመለከተ ለዩናይትድ ኪንግደም ስጋቷን ገለጸች
ማልዲቭስ የቻጎስ ደሴቶችን ሉዓላዊነት በተመለከተ ለዩናይትድ ኪንግደም ስጋቷን ገለጸች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.09.2026
ሰብስክራይብ

ማልዲቭስ የቻጎስ ደሴቶችን ሉዓላዊነት በተመለከተ ለዩናይትድ ኪንግደም ስጋቷን ገለጸች

​ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ሙዊዙ፤ ማልዲቭስ ከደሴቶቹ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና ባሕላዊ ትስስር በመጥቀስ፤ ዩናይትድ ኪንግደም የቻጎስ ደሴቶችን ለሞሪሸስ አሳልፋ ለመስጠት መወሰኗን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትር አንድሪው በርንሃም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

​ የማልዲቭስ መንግሥት ከቻጎስ ደሴቶች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር ገንቢ ግንኙነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ ነው፤ በተመሳሳይ የማልዲቭስን ግዛት እና የዜጎቿን ጥቅም ማስጠበቁን ይቀጥላል ብለዋል።

​ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሞሪሸስ ለአስርተ ዓመታት ከዘለቀ አለመግባባት በኋላ የቻጎስ ደሴቶች ሉዓላዊነት ለሞሪሸስ እንዲተላለፍ ቀደም ሲል ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በስምምነቱ መሠረት በዲያጎ ጋርሺያ የሚገኘው የዩናይትድ ኪንግደም-አሜሪካ የጦር ሠፈር ለ99 ዓመታት በሁለቱ ሀገራት ቁጥጥር ስር ይቀጥላል።

​ሆኖም ማልዲቭስ የባሕር ግዛቷን ሊጎዳ ይችላል በሚል ስጋት ዝውውሩን ተቃውማለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0