- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የቡና ንግድ እና የዕሴት መጨመር አብዮት፡ የአፍሪካ ሀብት በማን እጅ ይገባል?

የቡና ንግድ እና የዕሴት መጨመር አብዮት፡ የአፍሪካ ሀብት በማን እጅ ይገባል?
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቶች በጥሬ ዕቃነት ከአህጉሪቱ ወጥተው፣ በሌሎች አገራት የተለያዩ ሂደቶች ተከናውነውባቸውና የተጨመረ ዕሴት ተጨምሮባቸው ለገበያ ይቀርባሉ። ይህ አካሄድ አፍሪካ ከሀብቷ ሙሉ ጥቅም እንዳታገኝ ካደረጉ ተግዳሮቶች አንዱ ነው። የዕሴት ጭማሪ አብዮት ግን አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ባሻገር ወደ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ብራንድ ግንባታና ኢንዱስትሪ ባለቤትነት እንድትሸጋገር የሚያስችል ወሳኝ አቅጣጫ ነው።
"ቡናው በአብዛኛው በጥሬ ዕቃነት ይላካል፤ የዕሴት ጭማሪው ሥራ ግን ቡናው ከሚመረትበት ቦታ በጣም ርቆ በሌላ ስፍራ ይከናወናል። አብዛኛው ትርፍም የሚገኘው በዚያው ነው። በዚያም ይቀራል፤ ቡናው ወደሚመረትባቸው አገራት አይመለስም።" ሲሉ በዩጋንዳ የቡና ድርጅት ባለቤት የሆኑት ኤንድሬ ቬስትቪክ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ባሻገር የማቀነባበር፣ የብራንድ ግንባታና የኢንዱስትሪ ባለቤትነትን እንዴት ልታሳካ እንደምትችል እንቃኛለን። በዚህ ዙሪያም በዩጋንዳ የቡና ድርጅት ባለቤት ከሆኑት ከኤንድሬ ቬስትቪክ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0