- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

ከአህጉራዊ የፖሊሲ ቅንጅት እስከ ተቋማዊ ጥራትና ልማት

ከአህጉራዊ የፖሊሲ ቅንጅት እስከ ተቋማዊ ጥራትና ልማት
ሰብስክራይብ

ጥራት ማለት የአንድ ጊዜ ሥራ ብቻ ወይም የሆነ ወቅት ላይ ብቻ የሚሠራ በመሆኑ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፤ ጥራት ተቋማዊ ባህል መሆን አለበት። [….]በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የምታመርተው ምርት ወይም የምትሰጠው አገልግሎት ብቻውን በቂ አይደለም። ለአካባቢ ጥበቃና ለማኅበራዊ ገጽታ ምን አበርክተሃል? የሚለው ወሳኝ መመዘኛ ነው።"ሲሉ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት (EQAO) ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴውድሮስ መብራት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዚህኛውየአፍሪካን ሃይትስ /African Heights/ ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን የጋራ የኢኮኖሚ ውህደት ፈተናዎች እና የኢትዮጵያን ተቋማዊ የጥራትና የምርታማነት ጉዞ በጥልቀት እንመረምራለን።

📉 ክፍል አንድ፦ ብሔራዊ ፖሊሲዎችን ከአህጉራዊ ጥቅም ጋር ማጣጣም! በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት መምህር ከሆኑት ከአቶ አበራ ለሚ ጋር በመሆን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) የዞ የመጣቸውንዕድሎች እና ያሉበትን ተግዳሮቶች፣ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የህብረቱን የጋራ ዓላማዎች ከብሄራዊ እቅዶቻቸው ጋር እንዴት ማጣጣም እንዳለባቸው የዳሰስን ሲሆን፤

💡 ክፍል ሁለት፦ ጥራት እንደ ልማት መሠረት! የጥራት ሥርዓትን በተቋማት ውስጥ መዘርጋት ለሠራተኞች ደህንነት እና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ሽግግር ያለው ፋይዳ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የጥራት ባህልን በሀገሪቱ ተቋማት ውስጥ ለማስረጽ ምን ዓይነት ዕድሎችና ተግዳሮቶች ገጥመውታል? የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴውድሮስ መብራት ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡናል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0