በአኅጉሪቱ የአየር ንብረት ፈተናው እጅግ ከፍተኛ እየሆነና የሙቀት መጠኑም እየጨመረ ይገኛል - ናይጄሪያዊው ሳይንቲስት

ሰብስክራይብ

በአኅጉሪቱ የአየር ንብረት ፈተናው እጅግ ከፍተኛ እየሆነና የሙቀት መጠኑም እየጨመረ ይገኛል - ናይጄሪያዊው ሳይንቲስት

የአፍሪካ ሀገራት የካርቦን ልቀት መጠን ከ4% ያነሰ ቢሆንም ለአየር ንብረት ጉዳት በይበልጥ ተጋላጭ ሆነናል ሲሉ ናይጄሪያዊው የአካባቢና አየር ንብረት ሳይንቲስት ኤርነስት አፌሲማማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አክለውም "የፓሪስ ስምምነት ከ2015 ጀምሮ እስከ አሁን ባለው ከ10 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ በፋይናንስ ድጋፍ በኩል የተለወጠ ብዙ ነገር አለመኖሩ ግልጽ ነው። አፍሪካ ወደ ራሷ መመልከትና ራሷን መደገፍ ይገባታል ብዬ አስባለሁ፡፡ ሀብቷን መጠቀም፣ ከራሷ ጋር መነጋገር፣ እንዲሁም ትክክለኛውን ነገር በማድረግ በተለይም ከገጠማት አየር ንብረት የተጋላጭነት ሁኔታ መውጣት አለባት" ብለዋል።

ኤርነስት አፌሲማማ ከ14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረትና ልማት ጉባኤ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠየቅ ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች ለማግኘት ቪዲዮውን ይመለከቱ፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0