እንደበፊቱ አጀንዳ ተቀባዮች ሳንሆን አጀንዳ የምንፈጥር መሆን አለብን – የፓን አፍሪካ ፓርላማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት
18:15 08.09.2026 (የተሻሻለ: 20:24 08.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
እንደበፊቱ አጀንዳ ተቀባዮች ሳንሆን አጀንዳ የምንፈጥር መሆን አለብን – የፓን አፍሪካ ፓርላማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት
በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ አፍሪካውያን የሌሎችን ውሳኔ ተቀባይ ሳይሆኑ የውሳኔ ሃሳቦችን የሚያፈልቁ መሆን ይገባቸዋል ሲሉ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ተናግረዋል።
ዶ/ር አሽብር፣ ከ14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረትና ልማት ጉባኤ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠየቅ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
▪አንድነትና ዝግጅት፦ በቀደመው መንገድ መጓዝ ስላልጠቀመ አፍሪካ በአንድ ድምፅ፣ በአንድ ልብ እና አእምሮ ተዘጋጅታ የህዝቧን ጥቅም ለማስከበር በጋራ መሥራት ይኖርባታል።
▪ ተቋማዊ እርምጃ፦ "ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው" ብሎ ከመናገር ባለፈ ኤጀንሲዎችን እና ተቋማትን በማቋቋም በተግባር መሥራት ያፈልጋል።
▪ እኩልነትና ድርድር፦ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ሲኬድ እንደ በፊቱ በለማኝነት እና በበታችነት ሳይሆን እኩል መብት ባለው ተደራዳሪነት መቅረብ ይገባል።
የካርቦን ገበያና የተፈጥሮ ሀብት፦ ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በካርቦን ገበያው ተጠቃሚ ለመሆን አቅም ያላቸውን ትላልቅ ተደራዳሪዎችንና ሙያተኞችን ማዘጋጀት አለባቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X