ፑቲን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopiaፑቲን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት አስታወቁ
ፑቲን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.09.2026
ሰብስክራይብ
ፑቲን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት አስታወቁ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ፣ ፑቲን ከትራምፕ ጋር "አንድ ሠዓት የፈጀው" እና "በቀና መንፈስ የተካሄደ" የስልክ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

የሁለቱን መሪዎች ውይይት በተመለከተ የወጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፡-

🟠 በፑቲን እና በትራምፕ መካከል የተደረገው የስልክ ውይይት በግንባር ቀደምነት እና በግልፅነት የተካሄደ፣ እንዲሁም ምሥጢራዊነቱ የተጠበቀ ነበር፡፡

🟠 በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረገው ውይይት ትኩረቱን በዩክሬን ግጭት አፈታት ጉዳዮች ላይ አድርጎ ነበር፡፡

🟠 ትራምፕ በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው በዩክሬኑ ግጭት አፈታት ላይ ትልቅ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

🟠 ትራምፕ ከፑቲን ጋር ባደረጉት ውይይት የዩክሬን ግጭት በፍጥነት እንዲያበቃ የሚፈልጉ መሆኑን በግልፅ አብራርተዋል፡፡

🟠 ትራምፕ ለፑቲን እንደተናገሩት የዩክሬንን ግጭት ማስቆም በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ የሚስችል የዕድል በር ይከፍታል፡፡

🟠 ፑቲን አሜሪካ የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት የምታደርገውን የአሸማጋይነት ጥረት በቀና መልኩ ገምግመውታል፡፡

🟠 ፑቲን እና ትራምፕ የኩሽነር እና የዊትኮፍን ጉዞ በጥሩ ሁኔታ የገመገሙት ሲሆን፣ በዚህ መልኩ የሚደረገው ስራ ይቀጥላል፡፡

🟠 ፑቲን በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ሂደት ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር ተጨባጭ እና ዝርዝር ትንታኔ ለትራምፕ አቅርበዋል፡፡

🟠 ፑቲን በጦር ሜዳው ላይ ስላለው ግስጋሴ እና ሩስያ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ግቦችን ለማሳካት ያላትን አቋም ለትራምፕ አብራርተዋል፡፡

🟠 ፑቲን ሜላኒያ ትራምፕ የሩሲያ እና የዩክሬን ህፃናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡

🟠 ፑቲን በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ገንቢ የሆነ አጋርነት ለመገንባት የተያዘውን የትራምፕን ሀሳብ ደግፈዋል፡፡

🟠 ፑቲን ሩሲያ በአውሮፓ ላይ ምንም አይነት ጠብ የመጫር ዓላማ እንደሌላት ለትራምፕ ተናግረዋል፡፡

🟠 ሩሲያን በስጋትነት ለመፈረጅ የሚናፈሱት የተፈበረኩ ወሬዎች አውሮፓውያን ለዩክሬን የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማሳደግ እንደ ሽፋን የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

🟠 ፑቲን እና ትራምፕ በቀጣይም በተቀራረበ ግንኙነት ለመቀጠል ተስማምተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0