የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከሳዑዲው አቻቸው ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳውድ ጋር ተወያዩ
16:20 08.09.2026 (የተሻሻለ: 16:24 08.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከሳዑዲው አቻቸው ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳውድ ጋር ተወያዩ
ከውይይት በኋላ የወጡ የላቭሮቭ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
አረብ ሀገራት በአሜሪካ-እስራኤል የኢራን ግጭት ውስጥ ተስበው እንዲገቡ በመደረጋቸው ሩሲያ አዝናለች፡፡
የሁቲዎች በሳውዲ አረቢያ ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ፍሬ-ቢስ እና በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው፡፡
ሩሲያ የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት አሁንም ለድርድር ዝግጁ ነች፡፡
የአውሮፓ ሕብረት እና ኔቶ የሩሲያን ሽንፈት መፈለጋቸውን እና ዩክሬንን መደገፋቸውን ቀጥለውበታል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት የዩክሬን ቀውስ መንስኤዎች ውይይቶችን ለማስቀረት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል፡፡
በጋዛ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ሂደት ምንም አይነት መሻሻል አልታየም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X