ከሰው አልባ አውሮፕላኖች እስከ ከባድ መድፎች፦ ኢትዮጵያ በራስ አቅም የምታመርታቸው ወታደራዊ መሣሪያዎች

ሰብስክራይብ

ከሰው አልባ አውሮፕላኖች እስከ ከባድ መድፎች፦ ኢትዮጵያ በራስ አቅም የምታመርታቸው ወታደራዊ መሣሪያዎች

 

ኢትዮጵያ በራሷ ዕውቀትና የልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን የወታደራዊ መሣሪያዎች ማምረት መጀመሯን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጳጉሜን 3 “የጽናት ቀን” አስመልክቶ ባስተላለፉት የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክት ገልጸዋል።

 

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ በሀገር ውስጥ መመረት የጀመሩ የጦር መሣሪያዎች፦

 

🟠 ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች)፦ የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸው።

 

🟠 የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፦ ዘመናዊና ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የተገነቡ።

 

🟠 ከባድ መሣሪያዎችና መድፎች፦ የመከላከልና የማጥቃት አቅምን የሚያጎለብቱ።

 

🟠 ተተኳሽ ጥይቶች፦ በራሷ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች የሚመረቱ።

 

ዐቢይ አሕመድ፣ በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥቱ ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን ጀግኖች ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር እንደሚዘከርም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0