“መጪዎቹ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ያደጉ ሀገራት የሚጠየቁባቸው ሊሆኑ ይገባል” – የፓን–አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትሕ ጥምረት

ሰብስክራይብ

“መጪዎቹ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ያደጉ ሀገራት የሚጠየቁባቸው ሊሆኑ ይገባል” – የፓን–አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትሕ ጥምረት

የጥምረቱ፣ ሥራ አስፈጻሚ ሚቲካ ምዌንዳ፣ ጉባኤዎች ሌላ የተስፋ ቃል የሚገባባቸው ብቻ ሳይሆን ያደጉ ሀገራት የሚጠየቁባቸው ጭምር እንዲሆኑ ዛሬ መካሄድ በጀመረው 14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረትና ልማት ጉባኤ ላይ ጥሪ አቅርበዋል።

የተናጋሪው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 መጠየቅና መገምገም፦ ጉባኤው (ኮፕ32) ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ስብሰባዎች አፍሪካ ምን እንዳገኘችና እንዳጣች የምትጠይቅበት ሊሆን ይገባል።

🟠 ከቃል ወደ ተግባር፦ ወቅቱ አዲስ የተስፋ ቃል የሚሰጥበት ሳይሆን፣ ቀደም ሲል የተገቡ ቃሎች በተጨባጭ የሚተገበሩበት እንዲሆን አበክሮ መሥራት ያስፈልጋል።

🟠 የራሳችን ራዕይ፦ ስለ አኅጉራችን ያለን ራዕይ “ስብሰባ ከማስተናገድ የሰፋ እና በአፍሪካዊ ባለቤትነት ላይ የተመሠረተ” መሆን አለበት።

🟠 ተጠያቂነት ያለው አቋም፦ አፍሪካ በጉባኤዎቹ ምን እንደምትፈልግ፣ ለምን እንደምትፈልገው፣ እንዴት እንደምታሳካው፣ እና እራሷን እና ሌሎችንም ለውጤቱ እንዴት ተጠያቂ እንደምታደርግ ግልጽ አቋም ይዛ መቅረብ አለባት።

በስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ የተቀረጸ ቪዲዮ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0