"መርካተር" ካርታ መሻሩን ተከተሎ የአፍሪካ ሀገራት ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? ኢትዮጵያዊው ባለሙያ ያብራርሉ

ሰብስክራይብ

"መርካተር" ካርታ መሻሩን ተከተሎ የአፍሪካ ሀገራት ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? ኢትዮጵያዊው ባለሙያ ያብራርሉ

የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካን መጠን አሳንሶ የሚያሳየውን የ”መርካተር” ካርታ በመሻር በምትኩ የተሻሻለውን "ኢኳል ኧርዝ ካርታ"ን አጽድቋል፡፡

የውሳኔው ተግባራዊነት የሁሉም በተለይም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ርብርብ እንደሚጠይቅ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት የካርታ ሥራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ሊተኮርባቸው የሚገቡ ቁልፍ ነጥቦችን አንስተዋል፦

ሀገራዊና አኅጉራዊ ትግበራ፦ የአፍሪካ ሕብረት እና የየሀገራቱ የካርታ ኤጀንሲዎች አዲሱን ካርታ እንደ ግዴታ መከተል አለባቸው።

በትምህርት ሥርዓት ላይ ለውጥ ማድረግ፦ ተማሪዎች ለረጅም ጊዜ አሮጌውን ካርታ ሲማሩበት በመቆየታቸው የመማሪያ መጻሕፍትን መቀየርና ተከታታይ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል።

የአሮጌው ካርታ ተፈጠረውን ጉዳት መረዳት፦ ለተቀላጠፈ ትግበራ በዚህ የተዛባ ውክልና ምክንያት አኅጉሪቱ ስለተጎዳችው ነገር በወጉ መገንዘብ ግዴታ ነው፡፡

የአስተሳሰብ ለውጥ፦ የተዛባው ካርታ ያሳደረውን የሥነ-ልቦና ተጽዕኖ ለመቀየር ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ በትዕግስት መሥራት ይገባል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0