- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአፍሪካ የሰላም መዋቅር፡ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር

የአፍሪካ የሰላም መዋቅር፡ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር
ሰብስክራይብ

“[…] የአፍሪካ ህብረት እጅግ በጣም ጥሩ እና አወንታዊ ተፅዕኖዎችን ማሳደር ችሏል […] አፍሪካ ባለጠጋ አህጉር ናት። በዚህ አህጉር ውስጥ ብዙ ሀብት አለን፤ ነገር ግን እጅግ የበዛውን ሀብታችንን በህገ-ወጥ የፋይናንስ ፍሰቶች እናጣዋለን። በጣም ንቁ እና ብሩህ አእምሮ ያላቸው ህዝቦች አሉን፤ አጅግ በርካታ የሆኔ የወጣቶች ቁጥር አለን። የሚያስፈልገን የታረሰ እና የሚታረስ መሬት ሁሉ አለን፤ እንዲሁም የሚያስፈልጉን ዋና ዋና እና ወሳኝ የማዕድን ሀብቶች ሁሉ አሉን” ሲሉ ኤሊዝ ናልባንዲያን ልስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን ይዳስሳል። በቀዳሚው ጉዳዩ የአፍሪካ ህብረት ከዲፕሎማሲ ውይይት ወደ የዜጎችን ደህነት ጥበቃ የሚቀይርበትን እና የፋይናንስ ጥገኝነትን በመቀነስ የሰላም ስልታዊ አቅሙን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይቃኛል። በሁለተኛ ጉዳዩ ኢትዮጵያ የ 2029 ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ይዳስሳል። ለዚህም የብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጂራ አነጋግሯል። በሦስተኛው ጉዳዩ ደግሞ ጳጉሜን 1 የጀመረውንና እስከ ጳጉሜን 5 የሚዘልቅዉን ፌስቲቫል ይቃኛል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0