በባሕሬን የኢትዮጵያ ቆንስላ የ2019 አዲስ ዓመትን በድምቀት አከበረ
20:14 07.09.2026 (የተሻሻለ: 20:24 07.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በባሕሬን የኢትዮጵያ ቆንስላ የ2019 አዲስ ዓመትን በድምቀት አከበረ
በባሕሬን የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ከ500 በላይ ከሚሆኑ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት፣ የባሕሬን ወዳጆች፣ የአፍሪካ ሴቶች ማኅበር አባላት እና ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ጋር በመሆን የ2019 አዲስ ዓመትን በድምቀት አክብሯል።
ዝግጅቱ "ብዙሃነት፡ የኢትዮጵያ ውበት" በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን፣ የሀገሪቱን ባህላዊ ስብጥር፣ እሴትና የሰላማዊ አብሮ መኖር መንፈስ አጉልቶ የታየበት ስለመሆኑ ተመላክቷል።
በበዓሉ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃዎች፣ የቡና ሥነ-ሥርዓት እና የሁለቱን ሀገራት ማኅበረሰቦች ትስስር የሚያጠናክሩ የእንግዳ ተቀባይነት ዝግጅቶች ቀርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X