በምዕራባውያን ላይ የነበረው እምነት ለእስከ መጨረሻው አክትሟል - ላቭሮቭ
18:25 07.09.2026 (የተሻሻለ: 18:34 07.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በምዕራባውያን ላይ የነበረው እምነት ለእስከ መጨረሻው አክትሟል - ላቭሮቭ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴርጌ ላቭሮቭ ለሞስኮ ስቴት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኢንስቲትዩት ተማሪዎች እና መምህራን ያደረጓቸው ዋና ዋና ንግግሮች፡-
ሩሲያ የጥቅሞችን ሚዛን ያላከበረ ማንኛውንም ስምምነት በፍጹም አትቀበልም፡፡
ናዚዝም ወደ አውሮፓ በፍጹም ተመልሶ እንዳይመጣ የዩክሬን ግጭት ማብቃት አለበት፡፡
"ምዕራባውያን ሩሲያን ጠንካራ ሆና ማየት ወይም ከእኛ ጋር በታማኝነት መገናኘት በጭራሽ ፈልገው አያውቁም፡፡"
ምዕራባውያን ስደተኛ ሩሲያውያንን እንደ ፖለቲካዊ ኃይል ለመጠቀም የሚያደርጉት ጥረት "አሳዛኝ" ነው፡፡
አሜሪካ የሩሲያን አጋሮች ለመንጠቅ እና ለመለየት እየሞከረች ነው፡፡
ምዕራባውያን የሚመጣውን የሩሲያ የፓርላማ ምርጫ ለማስተጓጎል የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው፤ በምዕራባውያን ሀገራት ለሩሲያ ዜጎች የተዘጋጁ ከ60 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘግተዋል፡፡
የሩሲያ ዓለም አቀፋዊ አቋም እና የወደፊት ተፅዕኖ በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ውጤት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
ላቭሮቭ ጀርመን በቦን የሚገኘውን የሩሲያ ቆንስላ ለመዝጋት ያሳለፈችውን ውሳኔ "አስጸያፊ" ሲሉ ጠርተውታል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X