ከጥገኝነት ራስን ወደ መቻል፦ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር አዲስ ምዕራፍ

ሰብስክራይብ

ከጥገኝነት ራስን ወደ መቻል፦ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር አዲስ ምዕራፍ

የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሱ የሀገር ውስጥ መሐንዲሶችና ቴክኒሺያኖች ሙሉ የሎኮሞቲቭ ሞተሮችን፣ ቦጊዎችንና ፉርጎዎችን የማደስ ሥራ በሀገር ውስጥ ማካሄድ መጀመሩን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ዑማ ገልጸዋል።

የስኬቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ከውጭ ጥገኝነት ነፃ መሆን፦ ከዚህ ቀደም ለጥገና ወደ ውጭ አገር ይላኩ የነበሩ ባቡሮችና ፉርጎዎች አሁን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ እየታደሱ ነው።

🟠 ጊዜና ወጪን መቀነስ፦ በወራት የሚቆጠረውን የጥገና ጥበቃና የውጭ ምንዛሬ ወጪ አስቀርቷል።

🟠 የሀገር ውስጥ አቅም፦ የኢትዮጵያ እና የጂቡቲ ባለሙያዎች ትልቅ ኃላፊነት ሲሰጣቸው ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0