980 የነዳጅ ቦቴ ተሽከርካሪዎች ማሊ ዋና ከተማ ገቡ - የንግድ ዋና ዳይሬክቶሬት
11:20 07.09.2026 (የተሻሻለ: 11:24 07.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
980 የነዳጅ ቦቴ ተሽከርካሪዎች ማሊ ዋና ከተማ ገቡ - የንግድ ዋና ዳይሬክቶሬት
ይህ የነዳጅ መጠን ሀገሪቱ በነዳጅ አቅርቦቷ ላይ ያላትን ቁጥጥር እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን የማሊ የንግድ ዋና ዳይሬክቶሬት ገልጿል።
የነዳጅ ጭነቱ ቅዳሜ ዕለት ወደ ዋና ከተማዋ ባማኮ የገባው የማሊ ጦር ባደረገው ጥብቅ ጥበቃ እና አጃቢነት መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ አመላክቷል።
የነዳጅ ሥርጭቱና ማራገፉ ያለ እንከን እንዲከናወን ለማድረግ የጉምሩክ፣ የንግድ ዋና ዳይሬክቶሬት እና የብሔራዊ ፖሊስ አባላት የአየር ሁኔታ ሳይገድባቸው በቀንና በሌሊት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።
ቪዲዮው በንግድ ዋና ዳይሬክቶሬቱ የተለቀቀቅ ነው
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X