"ኢትዮጵያ ተነሥታለች ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
10:25 07.09.2026 (የተሻሻለ: 10:34 07.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"ኢትዮጵያ ተነሥታለች ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጳጉሜን 2 "የማንሠራራት ቀን" አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት፣ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ስኬት ከቃልና ከምኞት ባለፈ በተግባር የተረጋገጠ እውነት መሆኑን ገልፀዋል።
ዐቢይ፣ ዋና ዋና ፕሮጀክቶችንና የሪፎርም እርምጃዎችን ጠቅሰዋል፦
▪ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅና ውጤት
▪ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት ሥራዎች
▪ የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ
▪ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ
እነዚህ ለውጦች በዜጎች የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ እውነተኛ ብርሃን የፈነጠቁ መሆናቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለነገዋ ኢትዮጵያም ብሩህ ተስፋ የሚሰንቁ ታላቅ ርዕይ መሆናቸውን አመላክተዋል።
"ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም፡፡ በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።" ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X