- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የብሪክስ መስፋፋት፣ የደቡባዊ ዓለም ድምፅ እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ምላሽ

የብሪክስ+ (BRICS+) መስፋፋት፣የደቡባዊ ዓለም (Global South) ድምፅ እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ምላሽ
ሰብስክራይብ

የብሪክስ+ መስፋፋት የመጠን መጨመር ብቻ ሳይሆን የዓለም የጂኦ-ፖለቲካ እና የጂኦ-ኢኮኖሚ የኃይል ሚዛን ከምዕራባውያን የበላይነት ወደ ባለብዙ ዋልታ ሥርዓት እየተቀየረ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው። ለአፍሪካ ሀገራትም ምዕራባውያን ያዘጋጁትን የፖሊሲ አማራጭ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ አጋሮችን የመምረጥ አቅም ይሰጣቸዋል።” ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናት እና ምርምር ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ አበራ ኤሊያስ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ዝግጅታችን፦
· ብሪክስ+ እና የአዲሱ ዓለም ሥርዓት እውነታ፦ BRICS+ ከዓለም ህዝብ ቁጥር 45% በላይ እና ከነዳጅ ምርት 40% በላይ በመወከል በዓለም ኢኮኖሚ ላይ እያመጣ ያለውን መዋቅራዊ ለውጥ፤
· የአዲስ ልማት ባንክ የተግባር እርምጃዎች፦ ባንኩ ያለ ፖለቲካዊ ቅድመ-ሁኔታ የሚያቀርበውን ፋይናንስ፣ በሀገር ውስጥ ምንዛሬ ብድር የመስጠት እና በመሰረተ ልማት ላይ ትኩረት የማድረጉን ጥቅም፤
· የኢትዮጵያ ቦታ እና የጂኦ-ኢኮኖሚ ተፅዕኖ፦ ኢትዮጵያ በብሪክስ+ ውስጥ ያላትን የዲፕሎማሲ አቅም ፣ የህዳሴ ግድብ የኃይል ማከፋፈያ መስመሮችና የዲጂታል ኢኮኖሚን በNDB ፋይናንስ የመገንባት ዕድሎች፤ እንዲሁም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከአበራ ኤሊያስ(ዶ/ር) ጋር በስፋትና በጥልቀት ተመልክተነዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0