ግብፅን ጨምሮ የ8 ሀገራት፣ የእስራኤል ሚኒስትሮች ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማፈናቀል ያቀረቡትን ጥሪ ኮነኑ

ሰብስክራይብ

ግብፅን ጨምሮ የ8 ሀገራት፣ የእስራኤል ሚኒስትሮች ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማፈናቀል ያቀረቡትን ጥሪ ኮነኑ

የግብፅ፣ ኳታር፣ ዮርዳኖስ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኢንዶኔዢያ፣ ፓኪስታን፣ ቱርክ እና ሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማፈናቀል የሚደረጉ ጥሪዎች ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥሱ እና ቀጣናዊ መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥሉ መሆናቸውን አስጠንቅቀዋል።

የሚኒስትሮቹ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ለፍትሐዊ እና ዘላቂ ሰላም ያለው ብቸኛ መንገድ ምሥራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማዋ ያደረገች ሉዓላዊት የፍልስጤም ሀገር እ.አ.አ ሰኔ 4 ቀን 1967 ባገኘችው የድንበር መስመር መሠረት ማቋቋም መሆኑን አረጋግጠዋል።

🟠 አደገኛ የማፈናቀል ጥሪዎች "ማፈናቀልን በጥብቅ የሚቃወመውን" የትራምፕን የጋዛ የሰላም ዕቅድ በቀጥታ የሚፈታተኑ መሆኑን መግለጫው አፅንኦት ሰጥቷል።

በቅርቡ የእስራኤል የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ግቪር ለጋዛ የሰባት ዓመት በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ስደት ዕቅድ ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ቱርክ፣ ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሊላኩባቸው ከታሰቡ ሀገራት መካከል ይገኙበታል። የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ በበኩላቸው "ያለዚህ ስደት በጋዛ መጨረሻ ላይ እውነተኛ መፍትሔ ሊኖር አይችልም" ሲሉ ተናግረዋል።

በትራምፕ የሰላም ዕቅድ መሠረት የተተገበረው የአሁኑ የተኩስ ማቆም ስምምነት "ማንም ሰው ከጋዛ እንዲወጣ አይገደድም" እና "መውጣት የሚፈልጉ የመውጣት እንዲሁም የመመለስ ነፃነት አላቸው" የሚል ድንጋጌ ይዟል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘው ቪዲዮ በጋዛ ላይ ከተካሄደው የእስራኤል ጦርነት ከሦስት ዓመታት በኋላ ከፍርስራሽ ውስጥ የተገኙ የ100 ፍልስጤማውያን አስከሬኖች የመጨረሻ ስንብት ያሳያል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0