የአፍሪካ ሀገር በቀል ቋንቋዎች የንግድ ስትራቴጂ በመሆን የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን ይችላሉ - ናይጄሪያዊት ሥራ ፈጣሪ
የአፍሪካ ሀገር በቀል ቋንቋዎች የንግድ ስትራቴጂ በመሆን የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን ይችላሉ - ናይጄሪያዊት ሥራ ፈጣሪ
የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በግልጽ የሚታዩ ቢሆኑም ሳይስተዋሉ የቀሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞች ያሉባቸው ግዙፍ የገበያ ዕድሎች ናቸው ሲሉ በሩሲያ የሚገኝ የቱሪዝም ተቋም መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናይጄሪያዊቷ ሊሊያን ኤዚኔ ኦዞይግቦክዌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሥራ ፈጣሪዋ ስለ ሀገር በቀል ቋንቋዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት ላይ ስላላቸው ሚና ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 የውድድር ብልጫ፦ በደንበኞቻቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚግባቡ የንግድ ተቋማት ከፍተኛ እምነትን መገንባት፣ የደንበኛ ታማኝነትን ማሳደግ እና እስካሁን ያልተደረሱ አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘት ይችላሉ።
🟠 ቴክኖሎጂ እና ክህሎት፦ እንደ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚታገዙ አገልግሎቶች፣ የድምፅ ሞዴሎች እና የትምህርት ቴክኖሎጂ ያሉ አዳዲስ የንግድ ሞዴሎች እየተስፋፉ በመሆናቸው፤ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ባህላዊ እውቀትን ከዘመናዊ የቴክኖሎጂ ክህሎት ጋር ማጣመር የሚችሉ ባለሙያዎች ያስፈልጓታል።
🟠 የቋንቋ ሉዓላዊነት፦ በሀገር በቀል ቋንቋዎች የተደገፉ አሠራሮችን ማልማት የትምህርት፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የጤና ጥበቃ ዘርፎችን በመለወጥ በመጨረሻም የአፍሪካን ኢኮኖሚ ማጠናከር ያስችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X