የኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የ”ጎቤ” እና “ሽኖዬ” ባህላዊ ጨዋታዎች

ሰብስክራይብ
የክረምቱን መሰናበትና የብርሃኑን የበጋ ወራት መምጣት የሚያበስሩት የኦሮሞ ወጣቶች ባህላዊ ጨዋታዎች የሆኑት ጎቤ (የወንዶች) እና ሽኖዬ (የሴቶች) በአዲስ አበባ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተከበሩ ይገኛሉ።
እነዚህ የወጣቶች ጨዋታዎች በክረምቱ የወንዝ መሙላት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የአባ ገዳዎች ሽምግልና፣ የቤተ-ዘመድ መጠያየቅ እና ማኅበራዊ ግንኙነት ዳግም የሚጀመርበትን የብሩህ ወራት ጅማሮ ያውጃሉ።
በዓሉ አከባበር እና ባህላዊ ሥርዓቱ
🟠 ሥርዓተ ንስሐ (ጊና)፦ ከሰኔ 30 እስከ ነሐሴ 16 ባለው ጊዜ ውስጥ “አርዳ” (ሜዳ) ላይ እንጨት ይተከላል። ወጣቶች እርጥብ ሽንብራ በመያዝ ከአካባቢው ራቅ ወደሚል ተራራ በመውጣት “ጊና” (ንስሐ) ይገባሉ።
🟠 የምስጋና እና የፍቅር ጸሎት፦ ፈጣሪ (ዋቃ) ክረምቱን በሰላም አሳልፎ፣ በተራራቀው መካከል ፍቅርን፣ አንድነትን እና አቀራራቢነትን እንዲሰጥ ተማፅኖ ይደረጋል።
🟠 ቤት ለቤት ጨዋታ፦ ልመናቸው ሰምሮ ክረምቱ ሲወጣ ወጣቶቹ ጎቤ እና ሽኖዬ (አባቢሌ) እያሉ በመጨፈር ቤት ለቤት ይዘዋወራሉ።
ሽኖዬ፦የኦሮሞ ልጃገረዶች ልዩ ነጻነት
ልጃገረዶቹከወትሮው የተለየ ነጻነት እና ባህላዊ ኩራት አላቸው። “ቁኒ” (እንግጫ) ነቅለው፣ እጃቸውን በእንሾሽላ አስውበው እና ፀጉራቸውን “አደ-ጀሌ” ተሠርተው ያጌጣሉ። በመቀጠልም ቤት ለቤት በመዘዋወር እንግጫ እየሰጡ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ይገልጻሉ።
ማሳረጊያውን የኢሬቻ በዓል ያደረገው ደማቁ ጨዋታ
በገዳ ሥርዓት ባህላዊ እሴቶች ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸው እነዚህ ጨዋታዎች፦
▪️ የአዲስ ዓመት እና የመስቀል በዓላትን ተከትለው ይቀጥላሉ።
▪️ በመስከረም ወር በድምቀት በሚከበረው ታላቁ የኢሬቻ የምስጋና በዓል ላይ ማጠናቀቂያቸውን ያገኛሉ።
▪️ ወጣቶቹ ወደ ኢሬቻ ማክበሪያ ቦታዎች በመሄድ ባህላዊ ኩነታቸውን በምስጋና ያጠናቅቃሉ።
እንኳን አደረሳችሁ!
አዳዲስ ዜናዎች
0