በካቦ ቨርዴ በደረሰ የአውቶቡስ መከሰከስ አደጋ ብዙዎቹ ተማሪዎች የሆኑ ቢያንስ 21 ሰዎች ሕይወት አለፈ
15:45 06.09.2026 (የተሻሻለ: 15:54 06.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በካቦ ቨርዴ በደረሰ የአውቶቡስ መከሰከስ አደጋ ብዙዎቹ ተማሪዎች የሆኑ ቢያንስ 21 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በፎጎ ደሴት ላይ የተከሰተው የዚህ አደጋ መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆዜ ማሪያ ኔቨስ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስታውቀዋል። ቅዳሜ ዕለት በደሴቲቱ ደቡባዊ ክፍል አውቶቡሱ ከያዘው መንገድ ወጥቶ ወደ 30 ሜትር ያህል ጥልቅ ወደሆነ ገደል በመከስከሱ አደጋው ሊከሰት ችሏል።
በአደጋው ቢያንስ የ21 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ( አብዛኞቹ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸው) በርካቶች ደግሞ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አደጋው በደረሰበትና መሬት አቀማመጡ አስቸጋሪ በሆነ ሥፍራ የመታደግ ሥራው አሁንም የቀጠለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተጠቁሟል።
አደጋውን "ታላቅ ሰቆቃ" ሲሉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ለተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X