ኢራን እና አሜሪካ በነዳጅ ጫንቃ መርከቦች እና በወታደራዊ መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት አፋፋሙ
ኢራን እና አሜሪካ በነዳጅ ጫንቃ መርከቦች እና በወታደራዊ መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት አፋፋሙ
ነሐሴ 30 እና ጳጉሜን 1 አዳር፤ ኢራን በሁለት የአሜሪካ የባሕር ኃይል ጦር መርከቦች ላይ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ካስወነጨፈች በኋላ፣ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንቲኮም) ዳውኒ፣ ስታርክ 1 እና ካይሎ የተሰኙ ሦስት የነዳጅ ጫንቃ መርከቦችን ከጥቅም ውጪ ማድረጉን አስታውቋል።
የሴንትኮም አዛዥ አድሚራል ብራድ ኩፐር ጥቃቶቹ በቴህራን ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ለማሳደር ታስበው የተፈጸሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በምላሹ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ የተከለከለ የባሕር መስመርን በተጠቀሙ ሦስት የነዳጅ ጫንቃ መርከቦች እና የአሜሪካ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል። አብዮታዊ ዘቡ የአሜሪካን ጥቃት የትንኮሳ ድርጊት ሲል የኮነነ ሲሆን፤ መርከቦች ያልተፈቀዱ መስመሮችን እንዳይጠቀሙ ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን እንዳያደርጉ አስጠነቅቋል።
በተጨማሪም ማዕከላዊ ዕዙ የአሜሪካ ኃይሎች በኦማን ባሕረ ሰላጤ ውስጥ አንዲት የኢራን የነዳጅ ጫንቃ መርከብ መስመጣቸውን ዘግቧል።
በሌላ በኩል፣ የኢራኑ ፋርስ ኒውስ ኤጀንሲ እንደዘገበው፤ አብዮታዊ ዘቡ በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ የምትገኝ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ሰው-አልባ የውኃ ላይ ድሮን መምታቱን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X