የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
10:55 06.09.2026 (የተሻሻለ: 11:04 06.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጳጉሜን 1 “የእመርታ ቀን” ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ከልመናና ጥገኝነት በመላቀቅ እውነተኛ ሉዓላዊነቷን እያረጋገጠች መሆኗን ገልጸዋል።
ዐቢይ ፣ የሀገሪቱን ዋና ዋና እመርታዎችን ዘርዝረዋል፦
የስንዴ ምርት፦ ሀገሪቱ ለስንዴ ገቢ የምታወጣውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በማስቀረት በአፍሪካ ቀዳሚ አምራች ሆናለች።
ኢኮኖሚና ልማት፦ በ”ሌማት ትሩፋት” የምግብ ዋስትናን፣ በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ደግሞ የኢንዱስትሪና ሥራ ዕድል ዕድገትን ማረጋገጥ ተችሏል።
የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም፦ ቀደም ሲል “አይነኬ” የተባሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በቁርጠኝነት ተተግብረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ እነዚህ ስኬቶች ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ተቋቁማ ወደፊት መጓዟን የሚያሳዩና ለመጪው ዓመት ትልቅ ተስፋ የሰነቁ ናቸው ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X