አፍሪካውያን ለውበት ያላቸውን አመለካከት ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ማውጣት አለባቸው - ፓን-አፍሪካዊት

ሰብስክራይብ

አፍሪካውያን ለውበት ያላቸውን አመለካከት ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ማውጣት አለባቸው - ፓን-አፍሪካዊት

ቀጭን መሆንን የሚያስገድዱት የምዕራባውያን የውበት መለኪያዎች በአፍሪካውያን ሴቶች ላይ ጎጂ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው ሲሉ ፓን-አፍሪካዊቷ ጋዜጠኛና የፎር ዩ ሚዲያ ዳይሬክተር ዲያን ማኑዌላ ሲኬ ዱምቤ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ባለፉት ዓመታት ይህ የውበት ብያኔ በማኅበረሰባችን፣ በልዩ ልዩ የአፍሪካ ማኅበረሰቦች ዘንድ እንዲሰርፅ የተደረገ ሲሆን፤ እኛም ድርጊቱን እንደ መደበኛ ነገር አድርገን ተቀብለነዋል" ሲሉ ገልጸዋል።

በአፍሪካ ውስጥ ሴቶች በተለያዩ የሰውነት ቅርጾች እና መጠኖች ይገኛሉ፤ ቀጭን፣ ሞላ ደስ የሚል፣ ረጅም እና አጭር፤ ይህ ስብጥር ደግሞ የአህጉሪቱ ባለብዙ ቀለም ውበት እና ሀብት መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0