የአሜሪካ መልዕክተኞች የዩክሬንን ውዳሴ ናዚን ትኩረት ሰጥተውታል – የክሬምሊን ረዳት

© telegram sputnik_ethiopiaየአሜሪካ መልዕክተኞች የዩክሬንን ውዳሴ ናዚን ትኩረት ሰጥተውታል – የክሬምሊን ረዳት
የአሜሪካ መልዕክተኞች የዩክሬንን ውዳሴ ናዚን ትኩረት ሰጥተውታል – የክሬምሊን ረዳት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.09.2026
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ መልዕክተኞች የዩክሬንን ውዳሴ ናዚን ትኩረት ሰጥተውታል – የክሬምሊን ረዳት

“አሜሪካውያኑ ፕሬዝዳንታችን አጥብቀው ያሰመሩበትን አንድ ነጥብ ትኩረት ሰጥተው መመልከታቸው ሊጠቀስ የሚገባው ነው፤ ይህም የኪዬቭ አገዛዝ በጣም የታወቁ የናዚ ወንጀለኞችን አስከሬን እንደገና በመቅበር እውነተኛ ማንነቱን መሸሸግ ማቆሙን ነው” ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ፑቲን በውይይቱ ወቅት ዩክሬን የናዚ ወንጀለኞችን ማሞገሷን (ማክበር) በመቀጠሏ ላይ ትኩረት በማድረግ ጉዳዩን በግል አንስተዋል።

ቀደም ሲል የዩክሬን ብሔረተኞች ድርጅት (ኦዩኤን)* መሪ የነበረው ዬቭሄን ኮኖቫሌትስ በኪዬቭ አቅራቢያ በሚገኝ የመታሰቢያ መቃብር በክብር እንደገና ተቀብሯል። በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ፣ አዲሱ የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ዬቭሄን ኽማራ እና ሌሎች ከፍተኛ የኪዬቭ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

ናዚዎች በጀርመን ሥልጣን ሲይዙ ኮኖቫሌትስ ድላቸውን በደስታ ተቀብሎ ነበር። በ1930ዎቹ መባቻ ላይ ከአዶልፍ ሂትለር ጋር ሁለት ጊዜ በግል የተገናኘ ሲሆን የዩክሬን ብሔረተኞች የናዚን ዓላማ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

የአሁኑ የዩክሬን አመራር ኮኖቫሌትስን እንደ ብሔራዊ ጀግና የሚመለከተው ሲሆን፣ መንገድ በስሙ ይሰይማል፤ እንዲሁም ሥሙን ለወታደራዊ ክፍሎች እንደ የማዕረግ ክብር ይጠቀምበታል።

በርካታ ምዕራባውያን ፖለቲከኞች ዓይናቸውን ጨፍነው እያለፉት ቢሆንም ቅሉ፣ ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ የናዚ ወንጀለኞች መልሶ መቋቋም እና ውዳሴን ማየሉን በተደጋጋሚ ጠቁማለች።

* በሩሲያ የታገደ የሽብርተኛ ቡድን

 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0