የፑቲን፣ የዊትኮፍ እና የኩሽነር ውይይት “ፍሬአማ፣ ገንቢ እና ግልጽ” ነበር – የክሬምሊን ረዳት

© telegram sputnik_ethiopiaየፑቲን፣ የዊትኮፍ እና የኩሽነር ውይይት “ፍሬአማ፣ ገንቢ እና ግልጽ” ነበር – የክሬምሊን ረዳት
የፑቲን፣ የዊትኮፍ እና የኩሽነር ውይይት “ፍሬአማ፣ ገንቢ እና ግልጽ” ነበር – የክሬምሊን ረዳት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.09.2026
ሰብስክራይብ

የፑቲን፣ የዊትኮፍ እና የኩሽነር ውይይት “ፍሬአማ፣ ገንቢ እና ግልጽ” ነበር – የክሬምሊን ረዳት

 

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላዲሚር ፑቲን ከአሜሪካውያን አቻቸው ልዑካን ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር ጋር ያደረጉት ስብሰባ ለ3 ሠዓታት ከ10 ደቂቃ የቆየ ሲሆን፤ “ፍሬአማ፣ ገንቢ፣ እጅግ ግልጽ እና ምሥጢራዊ” እንደነበር የሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

 

ዋና ዋና ነጥቦች፦

 

🟠 ፑቲን የ ግጭቱን መነሻ መንስኤዎችን በሙሉ እልባት መስጠት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

 

🟠 ሩሲያ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ሁኔታ አስመልክቶ ዝርዝር ግምገማዎችን ያቀረበች ሲሆን፤ የሩሲያ ኃይሎች ግስጋሴ እና የተቀመጡት ዓላማዎች እንደሚሳኩ ያላቸውን እምነት አጉልታ አሳይታለች።

 

🟠 ፑቲን ለፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔዎች ከአሜሪካ ጋር አብሮ ለመሥራት ሩሲያ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

 

🟠 ዊትኮፍ እና ኩሽነር ዘላቂ እልባት ለመፈለግ በሚያደርጉት ጥረት ዛሬ በኪዬቭ በሚያደርጓቸው ግንኙነቶች የፑቲንን ግምገማዎች እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል።

 

🟠 አሜሪካውያኑ ልዑካን በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅተው እንደመጡና ወደ መፍትሔ ሊወስዱ የሚችሉ በርካታ ሐሳቦችን ማቅረባቸውን ኡሻኮቭ ገልጸዋል።

 

🟠 ፑቲን የኪዬቭ አገዛዝ ዋና ዋና የናዚ ወንጀለኞችን እንደገና መቅበር ጨምሮ የነበረውን ባህሪ ይበልጥ እያጋለጠ መሆኑን ተናግረዋል።

          

🟠 ውይይቱ ከዩክሬን ጉዳይ የተሻገረ ሲሆን፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ሊሆኑ የሚችሉ ግዙፍ፣ ለሁለቱም ወገኖች ጠቃሚ የሆኑ የሩሲያ-አሜሪካ ፕሮጀክቶችንም መርምሯል።

 

🟠 ፑቲን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ግላዊ ግንኙነታቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን፤ በዊትኮፍ እና ኩሽነር በኩል የሚደረገው ውይይትም በተመሳሳይ ይቀጥላል።

 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0