- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የአየር ንብረት ፍትሕ ትግል በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICJ) እና የአድዋ ድል ከፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ ጋር ያለው ትስስር

የአየር ንብረት ፍትሕ ትግል በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICJ) እና የአድዋ ድል ከፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ ጋር ያለው ትስስር
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ለዓለም አቀፉ የካርቦን ልቀት የምታበረክተው አስተዋፅኦ ከ4% በታች ቢሆንም፣ በድርቅ፣ ጎርፍና ረሃብ ምክንያት ግን ቀዳሚዋ ተጎጂ ሆናለች። ስለሆነም አፍሪካውያን የአየር ንብረት ድጋፍን እንደ የምዕራባውያን እርዳታና ምጽዋት መጠየቅ የለባቸውም፤ ይልቁንም በተበከለው አካባቢ ምክንያት በሕግ የተረጋገጠ የካሳ መብታቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያስከብሩ ይገባል።” ሲሉ የጂኦ-ኢንቫይሮመንት፣ የአየር ንብረት እና አዳፕቴሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ያዛቸው ውድነህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል

በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ (African Heights) ልዩ ዝግጅታችን፡
በክፍል አንድ፦ የአየር ንብረት ጉዳትን ወደ ሕጋዊ ካሳ የመቀየር አህጉራዊ ትግል፣ የበለፀጉ ሀገራት ሕጋዊ ተጠያቂነት በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICJ) ያለበትን ደረጃ እና የ"No-Harm" መርህንበማንሳት ከአቶ ያዛቸው ውድነህ ጋር በጥልቀት እንወያያለን፡፡
በክፍል ሁለት ደግሞ፦ በ1888 ዓ.ም የተጎናጸፍነው የአድዋ ድል በዓለም ዙሪያ ለሚኖሩ ጥቁር ሕዝቦች የፈጠረውን የነፃነትና የአንድነት መነቃቃት፣ የኢትዮጵያኒዝም ንቅናቄን፣ የማርከስ ጋርቬይን UNIA፣ የጋናውን ክዋሜ ንክሩማህ ጥረት እንዲሁም የአድዋ ድል ለ"ብላክ ፓንተር" ንቅናቄና ለዛሬው ዲጂታል ፓን-አፍሪካኒዝም የሰጠውን መንፈስ አስመልክቶ ከፓን-አፍሪካኒስት፣ ተመራማሪ እና ጋዜጠኛ ህይወት አዳነ ጋር ያደረግነውን ሰፊና ጥልቅ ውይይት እናቀርባላችኋለን፡፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0