በኢትዮጵያ የሕፃናት ከመጠን በላይ ውፍረት ምጣኔ 8.3% ደረሰ

© telegram sputnik_ethiopiaበኢትዮጵያ የሕፃናት ከመጠን በላይ ውፍረት ምጣኔ 8
በኢትዮጵያ የሕፃናት ከመጠን በላይ ውፍረት ምጣኔ 8 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.09.2026
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የሕፃናት ከመጠን በላይ ውፍረት ምጣኔ 8.3% ደረሰ

በኢትዮጵያ በሕፃናትና ታዳጊዎች ላይ የሚታየው ከመጠን በላይ መወፈር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች አስታወቁ።

የቀረቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

የሥነ-ምግብ ሦስትዮሽ ሸክም፦ ሀገሪቱ የምግብ እጥረት፣ የቫይታሚንና ማዕድን እጥረት እንዲሁም የከመጠን በላይ መወፈር ቀውስ ውስጥ ትገኛለች።

የመቀንጨር መጠን፦ የቀዳማይ ልጅነት የምግብ እጥረት ያስከተለው መቀጨር በሀገር አቀፍ ደረጃ 39% ደርሷል።

የስኳር አጠቃቀም፦ ከ6-23 ወር ባሉ ሕፃናት መካከል 31% በስኳር የበለፀጉ መጠጦችን የሚጠቀሙ ሲሆን በከተሞች በተለይም አዲስ አበባ፣ ሐረሪ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እስከ 50% ደርሷል።

የኢኮኖሚ ጉዳት፦ ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች በየዓመቱ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 1.8% (ከ31.3 ቢሊዮን ብር በላይ) ያሳጣሉ።

የሲቪል ማኅበራት ጥምረት ከፍተኛ ስኳር፣ ጨውና ቅባት ያላቸውን ምግቦች የሚቆጣጠር እና በምግብ ፓኬጆች ላይ ግልጽ ማስጠንቀቂያን የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ በአስቸኳይ እንዲጸድቅ መጠየቃቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0