የኢትዮጵያ የሥጋ ወጪ ንግድ ሽግግር፦ የቄራዎችን ምርት ወደ 46% የማድረስ ውጥን

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የሥጋ ወጪ ንግድ ሽግግር፦ የቄራዎችን ምርት ወደ 46% የማድረስ ውጥን

በእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት የወጪ ንግድ ቄራዎች፣ የሱማሌ ክልል እና የቦረና ዞን የእርድ እንስሳት ነጋዴዎች ማኅበራት አቅርቦትን በቀጥታ ለማገናኘት የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የሚከተሉትን እንዲያሳካ ይጠበቃል፦

የቄራዎችን ምርታማነት በአጭር ጊዜ ውስጥ አሁን ካለበት 10% ወደ 46% ማሸጋገር።

አርብቶ አደሩን፣ ነጋዴውን እና ቄራዎችን በቀጥታ በማገናኘት የደላሎችንና የሕገ-ወጥ ንግድ ማነቆዎችን መቅረፍ።

በሀገሪቱ የሚገኙ 17 የወጪ ንግድ ቄራዎች በዓመት እስከ 200 ሺህ ቶን ሥጋ ከማምረት አቅም ጋር የማይመጣጠነውን የ10% አቅርቦት ማሻሻል።

አሁን ላይ የአገር ውስጥ አቅርቦት ማነቆዎችን ከመፍታት ጎን ለጎን ተጨማሪ አዳዲስ የውጭ አገር የሥጋ ገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት ሰፊ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አመላክቷል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0