እናት በእንባ፣ አባት በእንብርክክ፤ ልጅ በናፍቆት

ሰብስክራይብ

#Viral | እናት በእንባ፣ አባት በእንብርክክ፤ ልጅ በናፍቆት

🫂 ሕጻን ፊዮና ሰለሞን ታግታ ከነበረችበት አካባቢ በፖሊስ ክትትል ነፃ ወጥታ ወደ ቤተሰቦቿ ስትቀላቀል የደስታ እንባን ያራጨ አቀባበል ተደርጎላታል።

ምን ተፈጠረ?

ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 አካባቢ በቦሌ ቡልቡላ አከባቢ ሕጻን ፊዮና ሰለሞን መቅደስ ሞገስ በተባለች የቤት ሠራተኛዋ ታግታ 3 ሚሊዮን ብር ተጠይቆባት ነበር።

የተወሰደው እርምጃ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዋን በጎንደር ከተማ ማራኪ ክፍለ ከተማ በቁጥጥር ስር በማዋል ሕጻኗን ታድጓል።

ከማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0