በዘላቂ ሥነ-ምኅዳራዊ ግብርና ውጤታማ የሆኑ ወጣቶች ተሸለሙ
08:04 05.09.2026 (የተሻሻለ: 08:14 05.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በዘላቂ ሥነ-ምኅዳራዊ ግብርና ውጤታማ የሆኑ ወጣቶች ተሸለሙ
የኢትዮጵያ ዘላቂ ሥርዓተ-ምግብና ሥነ-ምኅዳራዊ ግብርና ሕብረት በዘላቂ ሥነ-ምኅዳራዊ ግብርና ዘርፍ ተሰማርተው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ወጣቶች እውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል።
የሕብረቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ባዩሽ ጸጋዬ እንደገለጹት፣ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ የእውቅና መርሃ-ግብር በዘርፉ በመሰማራት ዘላቂ የሥራ እድል የፈጠሩ፣ የራሳቸውንና የማኅበረሰቡን ኑሮ ማሻሻል የቻሉ ወጣቶችን ለማበረታታት ያለመ ነው።
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም የእውቅና ሥነ-ስርዓቱ፡-
የወጣቶችን የግብርና ዘርፍ የፈጠራ ክህሎት ለማጎልበት፣
ዘላቂ የምግብ ሥርዓትና ሥነ-ምኅዳርን እውን ለማድረግ የሚደረጉ ሀገራዊ ጥረቶችን ለመደገፍ የጎላ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
በእውቅና እና ሽልማት መርሃ-ግብሩ ላይ ለተመረጡት ወጣቶች የገንዘብ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት እንደተበረከተላቸው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X