“ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን አሳንሰው የሚያሳዩ ካርታዎችን ትውልድ ማስተማሪያ አድርገዋል” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
19:35 04.09.2026 (የተሻሻለ: 19:44 04.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
“ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን አሳንሰው የሚያሳዩ ካርታዎችን ትውልድ ማስተማሪያ አድርገዋል” – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲቲዩት የካርታ ሥራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ካሳሁን እንደገለጹት፣ ለባሕር ጉዞ ተብሎ የተሰራው ነባሩ የ”መርካተር” ካርታ የሰሜንና ደቡብ ዋልታ ሀገራትን አግዝፎ፣ አፍሪካን ደግሞ እጅግ አሳንሶ ሲያሳይ ቆይቷል፡፡
ይህም በቴክኒክ ስህተት ብቻ ሳይሆን በቅኝ ገዢዎች ፍላጎት አስተሳሰብን ለመቅረጽ እንደ መሣሪያ ሲያገለግል እንደነበር፣ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካን ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ ካርታ ያጸድቃል ተብሎ መጠበቁን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
“ቀኝ ገዢዎች [ካርታውን] አሳንሶ ማሳያ አድርገው ይጠቀሙበታል። ስለዚህ ትልቁን አኅጉር ትንሽ አድርጎ በቃላት በተግባር ከመግለጽ ባሻገር ጭራሽ ታሪክ ሰርቶ፣ ውክልና አስቀምጦ ትውልድ ማስተማሪያ ሲደረግበት ነበር።” ሲሉ ቴዎድሮስ ተችተዋል፡፡
በዚህም አፍሪካ በካርታ ላይ አነስተኛ ተደርጋ እንድትሳል በመደረጉ በትውልዶች ላይ የይዘትና የታሪክ ጉዳት ማድረሱን መሪ ሥራ ስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X