ሩሲያ ዲጂታል ማጭበርበርን የሚታገሉ ወጣቶችን በማሰልጠን ኮንጎን ልታግዝ ትችላለች - መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሪ
16:55 04.09.2026 (የተሻሻለ: 17:04 04.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ዲጂታል ማጭበርበርን የሚታገሉ ወጣቶችን በማሰልጠን ኮንጎን ልታግዝ ትችላለች - መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሪ
ዲጂታል ማጭበርበር ለአፍሪካ ወጣቶች አደገኛ ስጋት ሲሆን፣ እሱን መታገል ደግሞ እንደ ኮንጎ ሪፐብሊክ ላሉ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፤ ሩሲያ ወጣት ኮንጎያውያንን እነዚህን ስጋቶች ለመከላከል እንዲችሉ በማሰልጠን ረገድ ልትረዳ ትችላለች ሲሉ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሪ ጆስሊን-ፓትሪክ ማንድዜላ በምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ተናግረዋል።
ኃላፊው የሚከተሉትን በርካታ የመፍትሔ እርምጃዎች አቅርበዋል፡-
▪ ስለ ዲጂታል ማጭበርበር ስጋቶች በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተዘጋጁ አጫጭር የትምህርት ሞጁሎችን ማበልጸግ፤
▪ ለላቀ ስልጠና ወደ ሩሲያ የሚላኩ ብቁ ወጣቶችን መለየት፤
▪ ዘላቂ እና የረጅም ጊዜ የማጭበርበር መከላከል አቅምን ለማረጋገጥ በኮንጎ ውስጥ የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ማብቃት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X