አሜሪካ በዊትኮፍ-ኩሽነር የሩሲያ ጉብኝት ወቅት ዩክሬን የሽብር ድርጊቷን እንዲታቆም ልትጠይቅ ትችላለች - ክሬምሊን
15:40 04.09.2026 (የተሻሻለ: 15:44 04.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አሜሪካ በዊትኮፍ-ኩሽነር የሩሲያ ጉብኝት ወቅት ዩክሬን የሽብር ድርጊቷን እንዲታቆም ልትጠይቅ ትችላለች - ክሬምሊን
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኞች የሆኑት ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር በሩሲያ በሚያደርጉት ጉብኝት ወቅት ይህ ማሳሰቢያ ሊሰጥ እንደሚችል ክሬምሊን አስታውቋል፡፡
"በዩክሬን ጉዳይ ሰላማዊ መፍትሄ ላይ የመድረስ እድልን ሙሉ በሙሉ ማግለል አይቻልም፤ ነገር ግን እስካሁን ለዚህ የሚሆኑ እርግጠኛ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች አልተፈጠሩም" ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
ሌሎች ዋና ዋና መግለጫዎች፡-
▫ ከዩክሬን ጋር በሚደረገው የሰላም ስምምነት ውሎች ላይ ሩሲያ ከሁለት ዓመት በፊት በፑቲን አማካኝነት ያቀረበችው አቋም አልተቀየረም፡፡
▫ በዩክሬን ግዛት ውስጥ የምዕራባውያንን መሳሪያዎች የሚያመርቱ ማናቸውም ተቋማት ለሩሲያ ኃይሎች ህጋዊ የጥቃት ኢላማዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡
▫ ሩሲያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ የረጅም ርቀት ሚሳኤል እና የድሮን ስርዓቶችን ለማልማት ስላሏቸው እቅዶች ሰምታለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X