የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናሚቢያ አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድ ለማቋቋም ድርድር ጀመረ - ዘገባዎች

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ አየር መንገድ በናሚቢያ አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድ ለማቋቋም ድርድር ጀመረ - ዘገባዎች
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናሚቢያ አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድ ለማቋቋም ድርድር ጀመረ - ዘገባዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.09.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናሚቢያ አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድ ለማቋቋም ድርድር ጀመረ - ዘገባዎች

የናሚቢያ ሥራና ትራንስፖርት ሚኒስትር ጆናስ ሼሎንጎ ሀገሪቱ አዲስ ብሔራዊ የአየር መንገድ ለማቋቋም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በስትራቴጂካዊ እና ቴክኒካዊ በትብብር ዙሪያ ውይይት እያደረገች መሆኑን አረጋግጠዋል።

የሁለትዮሽ ውይይቱ ከዚህ ቀደም "ኤር ናሚቢያ" የገጠመው የፋይናንስ ውድቀትና መዘጋት ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከልና ጠንካራ ብሔራዊ አየር መንገድ ለመገንባት ያለመ ነው ብለዋል።

"ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የተደረጉት ውይይቶች ትንታኔ ላይ ያተኮሩ እና ሰፊ የሆኑ የቴክኒክ እና የንግድ ጉዳዮችን ያካተቱ ናቸው። ሆኖም ከማንኛውም አካል ጋር ምንም አይነት አስገዳጅ ስምምነት አልተደረገም" ሲሉ በድርድሩ ዙሪያ የወጡ ይፋዊ ያልሆኑ መረጃዎችን ውድቅ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ሲል በቶጎ አስካይ አየር መንገድ፣ ኤር ኮንጎ፣ የማላዊ አየር መንገድ እና የዛምቢያ ኤርዌይስን ጨምሮ በአፍሪካ በርካታ አየር መንገዶች ምሥረታ ላይ አሻራውን ማሳረፉ የሚታወቅ ነው።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0